ፍጹምነት (እኽላስ) ያለው ደረጃ
    face
  •   
  •  
ጥበበኛው አላህ . .

Icreasefontsize decreasefontsize

ፍጹምነት (እኽላስ) ያለው ደረጃ

እኽላስ አቻ የሌለው የላቀ ደረጃ ያለው ሲሆን፣እኽላስ የሌለበት ሥራ ተቀባይነት የለውም። አላህ ﷻ ሥራችን እኽላስ እንዲኖረው ቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በብዙ አንቀጾች ያሳሰበ ሲሆን፣የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፦ ‹‹አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣. . እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)።›› [አልበይይናህ፡5]

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ስግደቴ፣መገዛቴም፣ሕይወቴም፣ሞቴም፣ለዓለማት ጌታ ነው በል። ለርሱ ተጋሪ የለውም፤በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ፤እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ (በል)።›› [አልአንዓም፡162-163]

በተጨማሪም አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ፣ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፤›› [አልሙልክ፡2]

በተጨማሪም እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በውነት (የተሞላ) ሲኾን አወረድነው፤አላህንም ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ ያጠራህ ኾነህ ተገዛው። ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው።›› [አልዙመር፡2-3]

አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦ ‹‹የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፣መልካም ሥራን ይሥራ፤በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ፣በላቸው።›› [አልከህፍ፡110]

   
Subscibe