የኢማን አስፈላጊነት
    face
  •   
  •  
ያዡ ለቃቂው አላህ . .

Icreasefontsize decreasefontsize

የኢማን አስፈላጊነት

አላህ ዘንድ ከሥራዎች ሁሉ በላጩና ተወዳሹ ኢማን ነው። ይህም አቡ ዘር (ረዐ) እንዲህ በማለት ለአላህ መልክተኛ ﷺ ባቀረቡትና በተሰጣቸው መልስ መሰረት ነው፦ ‹‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከሥራዎች ሁሉ በላጩ የትኛው ነው?›› ብለው ሲጠይቁ፣ነቢዩ ﷺ ፦ ‹‹በአላህ ማመንና በርሱ መንገድ መታገል ነው›› አሉ። (በሙስሊም የተዘገበ)

ወደ ቅኑ መንገድ ለመመራት፣የዱንያና ኣኽራን ተድላና ደስታ ለመጎናጸፍም መነሻ ምክንያት ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦ ‹‹አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለእስላም ይከፍትለታል፤›› [አልአንዓም፡125]

ኢማን አማኙን ከአላህ ትእዛዝ ጥሰት እንዲታቀብ ያደርገዋል። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦ ‹‹እነዚያ የተጠነቀቁት፣ከሰይጣን የኾነ ዟሪ በነካቸው ጊዜ፣(ጌታቸውን) ይገነዘባሉ፤ወዲያውም እነሱ ተመልካቾች ይኾናሉ።›› [አልአዕራፍ፡201]

ኢማን ሥራዎች አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ መሟላት ያለበት መስፈርት (ሸርጥ) ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ብታጋራ፣ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፤በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል።›› [አልዙመር፡65]

በጠራና ፍጹም በሆነ ኢማን አላህ ﷻ ሥራን ብሩክ ያደርጋል፣ጸሎትና ልመናንም እርሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደርጋል።

   
Subscibe