መልመጃ (በአላህ ማመን)
    face
  •   
  •  
በጣም ቅርቡ  አላህ . .

Icreasefontsize decreasefontsize

መልመጃ (በአላህ ማመን)

1-ሃይማኖትና ኢማን ከመንፈስ መረጋጋትና ከሕሊና ሰላም ጋር ያላቸውን ግንኙነት አብራራ።

2-የኢማንን ትርጉም ግለጽ፤በሕብረተሰቦች ላይ የሚኖረውን ተጽእኖና አሻራዎቹን ጥቀስ።

3-በአላህ ማመን የሚያስከትላቸው ግዴታዎችና መስፈርቶች ምንድን ናቸው?

4-አላህ ﷻ ዘንድ ከሥራዎች ሁሉ በላጩና ተመራጩ የትኛው ነው?

5-በአላህ ማመን፣በራስህ በቤተሰብህና በሕብረተሰብህ ውስጥ የተዋቸውን አሻራዎች፣ የተሰማህንና ያስተዋልካቸውን የኢማን ፍሬዎችም ዘርዝር።

6-በመልእክተኞች ማመን የሚያስከትላቸውና የሚጠይቃቸው ግዴታዎች ምንድን ናቸው?

7-ሶሓባን (ረ.ዐ) መውደድ በነቢዩ ሙሐመድ ﷺ የማመን አንድ አካል የሆነው ለምንድን ነው?

8-የቅያማ ቀን ትእይንቶችንና አስበርጋጊ ሁኔታዎችን፣ከመለስተኛ ምልክቶቹ አንስቶ የጀነት ሰዎች ወደ ጀነት፣የእሳት ሰዎችም ወደ አሳት እስከሚገቡበት ድረስ ያሉትን በቅደም ተከተላቸው መሰረት ግለጽ።

9-አንድን የአላህ አገልጋይ ወደ ጀነት ከሚያስገቡትና ከጀሀነም እሳት ከሚታደጉት ሥራዎች መካከል ዋነኞቹ የትኞቹ ናቸው?

10-በዕባዳዎችህ፣ለአላህ ባለህ ፍርሃትና በፍቅሩ ውስጥ የሚስተዋሉትን፣በመጨረሻው ቀን የማመንህን ፍሬዎች አብራራ።

11-ከጀነት ድሎት ታላቁ ድሎት የቱ ነው? ከጀሀነም እሳት ቅጣት ቀላሉ የቱ ነው?

   
Subscibe