በአላህ የማመን ጽንሰ ሀሳብና ትክክለኛ ምንነቱ
    face
  •   
  •  
ዐዋቂው፣ውስጠ ዐዋቂው፣በዕውቀት ከባቢው አላህ . .

Icreasefontsize decreasefontsize

በአላህ የማመን ጽንሰ ሀሳብና ትክክለኛ ምንነቱ

እውነተኛ ሃይማኖት የመንፈስ ሕይወትና የሚደሰቱበት የመዝናኛ ሜዳ ነው

የመንፈስ ደስታና የነፍስ እርካታ በአላህ ﷻ በማመን ብቻ እንጂ ሊገኝ አይችልም። ያላመነች ነፍስ የፈራች፣የባዘነች፣ደካማና ያልተረጋጋች ሆና ትቀራለች። ለመድህን የሚያበቃው ኢማን በአላህ ማመን ሲሆን፣ትርጉሙ አላህ ﷻ የሁሉም ነገር ጌታ፣ንጉሥና ፈጣሪ መሆኑን በቁርጠኝነት አምኖ ማረጋገጥ ነው። ሶላትን፣ጾምን፣ጸሎትን፣ተስፋ ማድረግን፣ፍርሃትን፣ መተናነስን፣ተገዥነትን . . የመሳሰለ የዕባዳ ዓይነት ለርሱ ﷻ ብቻ የሚገባ መሆኑን፣በሁሉም የምሉእነት በህርያት የሚገለጽ፣ከእንከንና ከጉድለቶች ሁሉ ፍጹም የጠራ መሆኑን ማመን ማለት ነው።

በአላህ ﷻ ማመን በመላእኮቹ፣በመልክተኞቹ፣በመጻሕፍቱ፣በመጨረሻው ቀን፣በጎውም ሆነ መጥፎው በርሱ ዕውቅናና በቅድመ ውሳኔው የሚከሰት መሆኑን ማመንን ያካትታል። ይህ እምነትም ለሰው ልጅ የደስተኝነትና የመታደል መሰረት ብቻ ሳይሆን፣ለአማኙ ሰው ፍጻሜው በአላህ ፈቃድ የኣኽራ ጀነት የሚሆን የዛሬ የዱንያ ሕይወት ጀነትም ነው።

በአላህ ማመን ወደ ፍትሕ የሚመራ ብርሃን ነው። ወደ ነጻነት የሚመራ ብርሃን ነው። ወደ እውቀትና ትምሕርት የሚመራ ብርሃን ነው። ወደ ቅን መንገድ የሚመራ ብርሃን ነው። ወደ ሕሊና እርካታና ወደ መንፈስ መረጋጋት የሚመራ ብርሃን ነው።

የኢማን ሸሪዓዊ ትርጉም ፦ በልብ አምኖ መቀበል፣በአንደበት መግለጽና በአካላት የእስላም ማእዘናትን መተግበር ሲሆን፣የታዘዙ ተግባራትን በመፈጸም ሲፋፋ በትእዛዛት ጥሰት ይቀጭጫል።›

ይህ ከታወቀ፣ሥራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ዋናው መሰረታዊ መስፈርት ኢማን ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏልና፦ ‹‹እርሱ ያመነ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች ማንኛውንም የሚሠራም ሰው፤።›› [አልአንቢያ፡94]

   
Subscibe