መልመጃ : (ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ የሆነውን አላህን ﷻ ዕወቅ)-(2)
    face
  •   
  •  
የሁሉ በላይ፣የላቀው የልዕልና ባለቤት አላህ . .

Icreasefontsize decreasefontsize

መልመጃ : ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ የሆነውን አላህን ﷻ ዕወቅ-(2)

1-የፍቅርን ትርጉም ግለጽ።

2-የአላህ ﷻ ፍቅር በአንተ ላይና በሕይወትህ ውስጥ የተወዋቸውን አሻራዎች ዘርዝራቸው።

3-አላህን ﷻ ያለ ፍርሃትና ያለ ተስፋ መጣል በፍቅር ብቻ ማምለክ ይቻላልን? መልስህን በነቢዮች ሁኔታ አስረጅነት አስደግፍ።

4-አላህ ﷻ አንድን ባሪያ ከወደደው ባሪያው ምን ያገኛል?

5-በምታውቃቸው የአላህ ስሞችና ባሕርያት (ስፋት) መካከልና በፍቅሩ መካከል ያለውን ትስስር አብራራ።

6-በአላህ ላይ ተስፋ መጣል (ረጃእ) ለሥራ ያበረታታልን? በቀጣዩ የአላህ ﷻ ቃል ላይ በመሞርከዝ አስረዳ ፦ ‹‹የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፣መልካም ሥራን ይሥራ፤በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ፣በላቸው።›› [አልከህፍ፡110]

7-በአላህ ላይ ተስፋ ማድረግ ማለት እርሱን አለመፍራት ማለት ነውን? ወይስ እርሱን መፍራት በርሱ ላይ ተስፋ መጣልን ያስከትላል?

8-በርሱ ላይ ተስፋ መጣልን (ረጃእን) የሚያስገኙና የምታውቃቸውን የአላህ ስሞችና ባሕርያቱን ጥቀስ።

9-ለአላህ ﷻ ያለህን ፍራቻ የሚጨምሩ ነገሮችን ጥቀሳቸው፣በቁጥር አስቀምጣቸው።

10-የርሱን ፍራቻ የሚያመጡና የምታውቃቸውን የአላህን ﷻ ስሞችና ባሕርያት ጥቀስ።

11-አላህን የሚፈራ ሰው ምን ማድረግ ይገባዋል?

12-ስነምግባርንና ተግባራትን የሚመለከቱ የዕባዳ አሻራዎች ፦ በጦሃራ - በሶላት - በዘካ - በጾም - በሐጅ ውስጥ ዋጂብ የሆነው ልክ ምንድነው?

13-የማይሰግድን ሰው ኢማን እንዴት ትመለከተዋለህ? መልስህን በማስረጃ አስደግፍ።

14-አንድ ሰው የሚሰግድ እየሆነ ሶላቱ ከመጥፎ ነገርና ከእኩይ ተግባር የማይከለክለው መሆኑ የሚታሰብ ነውን?

15-በአላህ ማመን ከልጆች፣ ከሚስት፣ከዘመዶች፣ከጎረቤቶችና ከሰዎች ሁሉ አያያዝ ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት ይገለጻል?

   
Subscibe