‹‹ላ እላሀ እልላሏህ›› በአማኙ ላይ የሚኖረው አሻራ
ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን መመስከር፣ለመስካሪው ፍሬ ያፈራል፤ ያጠራዋል፤ያንጸዋል። አላህን መውደድ፣ፈሪሀ
አላህ መሆን፣ተስፋውን መጠበቅና በርሱ ላይ መመካትን . . የመሳሰሉ የልብ ተግባሮችን የአማኙ ልብ እንዲያፈራ ያደርጋል።
በመስካሪው ግላዊም ሆኑ ማሕበራዊ ድርጊቶችና ሥራዎች ላይም፣‹‹ላ እላሀ እልላሏህ›› ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን
መመስከር፣የባለቤቱን ስነምግባርና አስተሳሰቡን በመቅረጽ፣ለአላህ ተገዥ የመሆንን ትርጉም እውን ያደርግ ዘንድ፣ልቡ ለአላህ
ፍጹም ታማኝ እንዲሆን በማድረግ አሻራውን ያሳርፍበታል። ዕባዳ (አምልኮተ አላህ) አላህ ﷻ የሚወዳቸውን ንግሮችና ተግባራት፣ግልጹንና
ስውሩንም ሁሉ የሚያካትት አጠቃላይ ጽንሰ ሀሳብ ሲሆን፣በግልጹ የአማኙ ተግባራት፣በስውሩ ውስጣዊ የስነልቦና ሁኔታዎቹና በባሕርያቱ
ላይ አሻራዎቹን ያሳርፋል። ዝርዝሩ እንደሚከተለው ይሆናል ፦