በስሞቹና በባሕርያቱ ማመን በባሪያው ላይ የሚያሳርፈው አሻራ
    face
  •   
  •  
ልመናን ተቀባዩ አላህ . . .

Icreasefontsize decreasefontsize

በስሞቹና በባሕርያቱ ማመን በባሪያው ላይ የሚያሳርፈው አሻራ

1-በአላህ ﷻ ስሞችና በባሕርያቱ እርሱን ማምለክ፦ አንድ አገልጋይ ስሞቹንና ባሕርያቱን ካወቀ ጌታው በሚፈልገው መንገድ ያምንባቸዋል። በጌታው ያለውን እምነት በሚያሳድግ ሁኔታ ትርጉማቸውን ይረዳል።እርሱን ባወቀ ሰው ልብ ውስጥ የአላህ ﷻ ኃያልነትና ግርማ ሞገሱ ስር ይሰዳል። ለዚህ ነው ‹‹አላህን ይበልጥ የሚያውቅ ከማንም ይበልጥ እርሱን ይፈራል›› የተባለው።

2-የኢማን መጨመር ፦ የአላህን ﷻ መልካም ስሞችና የላቁ ባሕርያቱን ማወቅ፣የአላህን ﷻ ኃያልነትና ግርማ ሞገሱን የመገንዘብ ስሜት በአገልጋዩ ልብ ውስጥ እንዲፈጠር ያደርጋል። ይህም በኢማኑ ላይ ኢማንን፣ለአላህ ﷻ ባለው መተናነስና ተገዥነት ላይ የበለጠ መተናነስንና ተገዥነትን ይጨምርለታል። ‹‹እነዚያም የተመሩት፣(አላህ) መመራትን ጨመረላቸው፤›› [ሙሐመድ፡17]

3-የአላህ ﷻ ውዳሴ ፦ አላህን ያወቀ ሰው ይወደዋል፤ጌታውን የወደደ ሰው ደግሞ፣ልቡ ሙሉ በሙሉ ለፍቅሩ የተገዛ በመሆኑ የርሱን ውዳሴ ያበዛል። ውዴታው ሌሎችን ለርሱ ብቻ ብሎ እስከመውደድና ለርሱ ብቻ ብሎ እስከመጥላት ደረጃ ይዘልቃል።

4-አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፦ ‹‹ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባላንጣዎችን (ጣዖታትን)፣አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፤እነዚያ ያመኑትም፣አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፤›› [አልበቀራህ፡165]

አንድ አገልጋይ የአላህን ﷻ ባሕሪ ኃያልነት ሲያውቅ ነፍሱ ወደ ጌታው ታዘነብላለች፤በርሱም ﷻ ትንጠለጠላለች። በግርማ ሞገሱና በውበቱ ምሉእነት ነፍሱ ትፈነድቃለች። በዚህም አገልጋዩ በአልረሕማን ንግግር (በቁርኣን) ጥፍጥና ይደሰታል፤እርሱን በመጥራት፣ተስፋውን በርሱ ላይ በመጣልና እርሱን ብቻ በመፍራት ይጽናናል። የአላህ ﷻ ውዴታ ወደዚያ የሚገፋፋው በመሆኑ አላህን ሲወድ፣አላህ የሚወደውን ነገርና አላህ የሚወደውን ሰው ሲወድ እናገኛዋለን።

5-አላህን ﷻ ማፈር ፦ አንድ አገልጋይ አላህን ﷻ ባወቀ ቁጥር የበለጠ ያከብረዋል፣ያልቀዋል። የበለጠ ባከበረውና ባላቀው መጠንም እርሱን ማፈሩ ይጨምራል፤ሞትን አስታውሶ ያለቅሳል፤አካላቱን አላህ ﷻ ከማይወደው ነገር ይጠብቃል።

ማንም ሰው የአላህን ﷻ እርሱነትና ባሕርያቱን በተመለከተ እርሱ ራሱን ከገለጸበት ውጭ በምንም ነገር እርሱን መግለጽ የለበትም። እርሱን አስመልክቶ በገዛ ሀሳቡ ምንም ነገር ማለት የለበትም፤እርሱ የልቅና ባለቤት የሆነ የጠራ የዓለማት ጌታ ነውና።

ኢማም አቡ ሐኒፋ

6-ራስን ለርሱ ማስተናነስና ለርሱ ማደግደግ፦ የአላህን ﷻ ኃያልነት ካወቅህ የራስህን ኢምንትነት ታውቃለህ። የርሱን አቅምና ችሎታ ካወቅህ ያራስህን ደከማነት አውቀህ ትቀበላለህ። የርሱን ፍጹማዊ መብቃቃት ካወቅህ የራስህን ድህነት ታውቃለህ። የርሱን ፍጹማዊ ምሉእነት ካወቅህ የራስህን እንከንና ጉድለት ታውቃለህ። የባሕርያቱን ምሉእነትና የስሞቹን ውበት ካወቅህ፣አንተ ተገዥ ባሪውያው እንጅ ሌላ አይደለህምና የራስህን ጉድለት፣ድህነት፣ደካማነትና አቅም የለሽነት ትገነዘባለህ።

   
Subscibe